2.1: አዲስ ክምችት መፍጠር

አዲስ ክምችት ለመፍጠር ከ“ፋይል” ምናሌ ውስጥ “አዲስ” የሚለውን ምረጥ። ብዙ የሚሞሉ መስኮች ይኖራሉ -- የእነዚህን ዋጋዎች በቅርጽ እይታ መቀየር ይችላል።

“ክምችት ርዕስ” በክምችቱ መነሻ ገፅ ላይ ላይ የሚታይ ጽሁፍ ነው። መጠኑ የቱንም ሊሆን ይችላል።

“የይዘት ገለጣ” ክምችቱን በተቻለ መጠን በዝርዝር መግለጽ አለበት። ይህንን በፓራግራፍ ለመከፋፈል የመግቢያ ቁልፉን ተጠቀም።

በመጨረሻ አዲሱ ክምችት ቀደም ሲል ካለው ክምችት ጋር ተመሳሳይ እይታ እና ሜታዳታ እንዲኖረው መግለፅ ያስፈልጋል ወይም በነባሪ እንዲጀምር “አዲስ ክምችት” ላይ ማድረግ ይቻላል። አዲስ ክምችቶችን ነባሪ ላይ ማድረግ መደበኛ ውቅር እና ደብሊን ኮር ሜታዳታ እንዲኖር ያስችላለል። በኋላ እነዚህን መቀየር ይቻላል።

“ይሁን” የሚለውን በመጫን ክምችቱን ፍጠር።

“ሰርዝ” የሚለውን ከተጫንክ ወደ ዋናው ማያ ወዲያውኑ ይመልሳል።