8.8: የዲፖዚተር ሜታዳታ

ግሪንስቶን ዲፖዚተር ተጠቃሚዎች አዲስ ሰነዶችን በድር በይነገጽ ወደ ክምችት እንዲያስገቡ ያስችላቸዋል። በዚህ ክፍል ውስጥ የዲፖዚተር ሜታዳታ ንጥልን የምንመለከት ሲሆን የትኞቹ ሜታዳታ መስኮች አዲሶቹን ሰነዶች በዲፐዚተር መጨመር እንደሚቻል ያስረዳል። ማንኛውም ሜታዳታ ስብስቦች ከአሁን ክምችት ጋር ተያያዥ የሆኑት ሜታዳታ ስብስቦች ለምርጫ ይቀርባሉ። በክምችቱ ውስጥ ከ"ግሪንስቶን ኤክስትራክትድ ሜታዳታ ስብስብ" በቀር ሌላ ተያያዥ ሜታዳታ ስብስብ ከሌላ የ"ዱብሊን ኮር ሜታዳታ ስብስብ" እንደ ነባሪ አገልግሎት ላይ ይውላል። የበለጠ ስለዲፖዚተር ለማወቅ ከፈለግህ http://wiki.greenstone.org/wiki/gsdoc/tutorial/en/depositor.htm ላይ “ፎርማት” በሚለው ትብ ስር “ዲፖዚተር ሜታዳታ” ተጫን።

ዲፖዚተር ሜታዳታ ውስን ቦታ ያሉትን ሜታዳታ መስኮች በዝርዝር ያቀርባል። ከክምችቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ከአንድ በላይ ሜታ ዳታ ስብስብ ከሆኑ፣ ተጎራባች ሜታዳታ ስብስቦች በተለያዩ ከለሮች ይቀርባሉ።መዳፊቱን በታዳታ ኤለመንት ላይ ማነዣበብ፤ ይህንን መግለጫ የሚያሳይ አስረጅ ይቀርባል።

በዲፖዚተር ተጠራቅመው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ የምትፈልጋቸውን አዲስ ሰነዶች መርምር። የተቆልቋይ ዝርዝር ከሁለት ምርጫዎች ጋር ከተመረጡ ኤለመንቶች ጎን ይቀርባል። በድር በይነገጽ ላይ ምን ዓይነት ግቤት ሳጥን (input box) መጠቀም እንዳለብህ ያስችላል። “ጽሁፍ” ማለት ነጠላ መስመር ግቤት ሳጥንን ለመጠቀም ሲሆን “ጽሁፍ ስፍራ” የሚለው ደግሞ ባለብዙ መስመር ግቤት ሳጥን መጠቀም ማለት ነው። ለእያንዳንዱ መስክ ተገቢውን የሳጥን አይነት ምረጥ።

ቢያንስ አንድ ሜታዳታ ኤለመንት መምረጥ ያስፈልጋል። ከዝርዝሩ የተመረጠው አንድ ኤለመንት ብቻ ከሆነ፣ የተመረጠውን መልሰህ ስታጠፋ (de-selecting) ብቅ ባይ ማስጠንቀቂያ መልዕክት፤ "At least one metadata element should be selected." ይመጣል።