9.3: ክምችቶችን ወደሌላ ቅርጸት መላክ |
ግሪንስቶን የሜታዳታ ይዘቶችን ወይም ክምችቶችን ወደተለያዩ መደበኛ ቅርጾች ማለትም እንደ METS, DSpace እና MARCXMLመላክ ይችላል።
አንድም ክምችት ለመላክ ከ“ፋይል” ምናሌ “ላክ…” የሚለውን ይምረጡ። የትኛውም ቅርጽ መላክ እንደምትፈልግ በመምረጥ እና “ወደዚህ ላክ” ተቆልቋይ ዝርዝሩ ውስጥ መምረጥ ያስፈልጋል። የተላኩትን ፋይሎች የሚቀመጥበት አቃፊ ስም ስጥ— ፋይሎቹም <ዱካ ወደ greenstone>/tmp/exported_xxx, በሚል ይጨርሳሉ፣ xxx የሰጠኸው ስም ይሆናል። ክምችቶች አንዱን በመምረጥ “ክምችት ላክ” የሚለውን ተጫን።
ለተለያዩ ቅርጸቶች የሚሆኑ የተወሰኑአማራጮች አሉ። የኤክስኤስኤልቲ (XSLT) ፋይሎችን በመሰየም ኤክስኤምኤል ሰነድ እንዲሰጡ ማድረግ ይቻላል። ወደ ማርክኤክስኤምኤል (MARCXML) ለመላክ ግሪንስቶን ሜታዳታ ወደ ማርክ መስክ ማፕ የሚያደርግ የማፕ ፋይል ያስፈልጋል። ነባሪው ማፒንግ ፋይል ማፕ የሚደርገው ዱብሊን ኮር ሜታዳታ ብቻ ነው። ማፒንግ ፋይል እራስህም አበጅተህ መጠቀም ትችላለህ።