9.4: ክምችቶችን ወደ ሲዲ/ዲቪዲ መላክ |
ግሪንስቶን አንድ ወይም ከዚያ በላይ ክምችቶችን በራስ ተነሳሽ ሲዲ/ዲቪዲ ዊነዶውስ መላክ ይቻላል።
አንድን ስብስብ ወደሌላ ሲዲ/ዲቪዲ ለመላክ ከ“ፋይል” አዶ “የሲዲ/ዲቪዲ ምስል ጻፍ” የሚለውን ተጫን። ከዚያም የግሪንስቶን ክምችቶች ሲመጡ መግለጫውን በመምልከት የሚላኩትን ስብስቦች ምረጥ። “የሲዲ/ዲቪዲ ስም” በሚለው ውስጥ የሲዲ/ዲቪዲ ስም ፃፍ። ይህም በስታርት ሜኑ ውስጥ ሲዲ/ዲቪዲ ሲጫን የሚታይ ነው። የተሰራው ሲዲ/ዲቪዲ በቀጥታ ከዲስክ ድራይቭ የሚሰራ መሆኑን ወይም ፋይሎችን ኮምፒውተሩ ላይ ኢንስቶል ማድረግ እንዲችል መምረጥ ይችላሉ። ከዚያም “የሲዲ/ዲቪዲ ምስል ጻፍ” የሚለውን ተጫን። ሂደቱ ብዙ ፋይሎች ስለሚቀዳ ጥቂት ደቂቃዎች ሊፈጅ ይችላል።
ሲያልቅ፣ ግሪንስቶን የተላኩትን ክምችቶች የያዘውን አቃፊ ስም ያሳያል። ከዚያም ወደ ሲዲ/ ዲቪዲ ለመገልበጥ ባዶ ሲዲ ወይም ዲቪዲ ተጠቀም።