9.2: ፋይልን ማዛመድ |
የላይብረሪያን በይነገጽ የተለዩ የፋይል አይነቶችን ለመክፈት የተለየ አፕሊኬሽን ይጠቀማል። የፋይል ዝምድናውን ለመቀየር “ፋይል” የሚለውን አዶ በመክፈት “ፋይል ማዛመድ…” የሚለውን ተጫን።
ዝምድና ለመጨመር የሚመለከተውን ፋይል ቅጥያ ከዝርዝር ውስጥ በመምረጥ ወይም አዲስ ቅጥያን በመፃፍ ይሆናል (“.” አትጨምር)። ከዚያም የሚመለከተውን አፕሊኬሽን ትእዛዝ በተገቢው ቦታ በመፃፍ ወይም አፕሊኬሽኑን “ብሮውዝ” ከሚለው መገናኛ መምረጥ ይችላል። “1%” የተከፈተው ፋይል ስም ለመጠቀም ትእዛዝ መስጠት ይቻላል። አንዴ እነዘህ ከተሟሉ “አክል” መንቃት ስለሚችል ዝምድናውን መጨመር ይቻላል።
ዝምድናውን ኤዲት ለማድረግ ያለውን ፋይል ቅጥያ ምረጥ። ማንኛውም ዝምድና ያለው ትእዛዝ “ትዕዛዝ አስነሳ” በሚል መስክ ይታያል። ኤዲት አድርገው ከዚያ “ ተካ” የሚለውን ተጫን።
ዝምድናውን ለማስወገድ ያለውን ፋይል ቅጥያ በመምረጥ “አስወግድ” የሚለውን ተጫን።
የፋይል ዝምድናዎች የሚጠራቀሙት በላይብረሪያን በይነገጽ ዋና አቃፊ ውስጥ ሲሆን የፋይሉ ስም "associations.xml" ነው።