4.8: ዛፎቹን ማጣራት |
ክምችትን “ማጣራት” እና የስራቦታ ዛፎቹን ማጣራት የተወሰኑ ፋይሎችን ለመፈለግ ፍለጋው እንዲጠብ ያደርጋል።
የ“ፋይሎችን አሳይ” ተዘርጋፊ ምናሌ ከእያንዳንዱ ዛፍ ስር የሚያሳየው ቀደሞ የተሰየሙ ማጥሪያዎችን፣ ማለትም “ምስሎች” ያሉትን ነው። ይህንን መምረጥ ሌሎች በዛፍ ውስጥ ያሉ ፋይሎች ለጊዜው እንዲደበቁ ያደርጋል። ዛፉን እንደገና ለመመለስ ማጣሪያውን ወደ “ሁሉም ፋይሎች” ማምጣት ነው። እነዚህ ተግባሮች ክምችቱን አይቀይሩም፣ በዛፉ ውስጥ ያሉትን አቃፊዎች ላይ ተፅእኖ አያደርሱም።
ፋይሎችን ለማዛመድ ሀረግ በመጻፍ ብጁ ማጣሪያ መሰየም ይቻላል (ለላይብረሪያን እና ኤክስፐርት ሁነታዎች ብቻ)። መደበኛ የፋይል ስርአት ማሳጠሪያዎችን ማለትም "*.doc" ("*" ማንኛውንም ሕብረቁምፊ ይዛመዳል) ብቻ ተጠቀም።