8.4: ባህሪይ ቅረጽ

ግሪንስቶን ስትጠቀም የምትመለከታቸው ድረ ገጾች ቅድሚያ ያልተቀመጡ ነገር ግን በምትጠቀምበት ጊዜ እንደአስፈላጊነቱ የሚፈጠሩ ናቸው። እነዚህን ገጾች ለመለወጥ የቅርጽ ትእዛዝ (ፎረማት ኮማንድ) መስጠት ያስፈልጋል። በዚህም አንድ ሰነድ ሲታይ የሚወጡ አዝራሮች እና በDateList ክላሲፋየር መቅረብ ያለባቸው የትኞቹ እንደሆኑ ተፅእኖ ያደርጋል። የቅርጽ ትእዛዝ ማዘጋጀት ቀላል አይደለም። ስለሆነም የግሪንስቶን አደራጅ መምሪያ ምዕራፍ ሁለት ማንበብ ይኖርብዎታል። በዚህ ክፍል ውስጥ የቅርጸት አዘገጃጀት እና እንዴት በላይብረሪያን በይነገጽ በኩል እንደሚገቡ ያስረዳል። “ቅርፀት” በሚለው ትብ ስር “ባህሪይ ቅረጽ” የሚለውን ተጫን።

የቅርጽ ትእዛዞችን በማንኛውም “ባህሪ ምረጥ” ተዘርጋፊ ዝርዝር ስር ላይ ማስተላለፍ ይቻላል፣ ይህም እያንዳንዱን ክላሲፋየር እና ቅደሚያ የተሰየሙ የባህሪ ዝርዝርን ያካትታል። አንድን ባህሪ ስትመርጥ ሁለት አይነት የቁጥጥር ሂደቶች ታገኛለህ። አንዳንድ ባህሪዎች በቀላሉ ማንቃት ወይም አለማንቃት የሚቻል ሲሆን ይህም በቼክ ቦክስ የሚደረግ ቁጥጥር ነው። ሌሎቹ መገለፅ ያለበት የቅርጽ ሕብረቁምፊ ይፈልጋሉ። ለእነዚህ ከዝርዝሩ ወደታች (“ተጽኖ የሚደረግበት አካል”) በመምረጥ የትኛው ባህሪ ሕብረቁምፊው እንደሚጠቀሙ በመምረጥ በጽሁፍ ቦታው (“ኤችቲኤምኤል ቅርጽ ሕብረቁምፊ”) ላይ ቅድሚያ የተሰየሙ “ተለዋዋጮች” የሚለውን ምረጥ። በቅርጽ ሕብረቁምፊፎ ተለዋዋጭ ለማስገባት ጠቋሚውን ወደሚገባበት ቦታ ላይ በማስጠጋት ከዚያም የተፈለገውን ተለዋዋጭ ከ "Insert Variable..." ጥምድ ሳጥን ውስጥ ምረጥ።

"ሁሉም ባሕሪያት" በመምረጥ ለአንድ አካል ነባሪ ቅርጽ መሰጠት ይቻላል። ይህ ቅርፀት ለሁሉም ባህሪያት ተፈፃሚ የሚሆን ሲሆን የተለየ ባህሪ ካልተሰጠው በስተቀር ለሁሉም ይህንኑ ይጠቀማል።

አዲስ የቅርጽ ትእዛዝ ለማከል፣ ሊሆን የሚችለውን ባህሪ እና አካል ምረጥ። ለዚህ ትእዛዝ ነባሪው ዋጋ ግራጫ ሆኖ ይታያል። ይህንን ወደ ክምችት ለመጨመር "Add Format" የሚለውን ተጫን። ከዚያም “ኤችቲኤምኤል ቅርጽ ሕብረቁምፊ” ለማስተካከል እንዲቻል ይሆንና ከተፈለገ ማስተካከል ይቻላል። ለእያንዳንዱ ባህሪ/አካል አንድ ቅርጽ ብቻ መስጠት የሚቻለው።

አንድን የቅርጽ ትእዛዝ ለማስወገድ፣ ከዝርዝሩ ውስጥ ምረጥና “ቅርጽ አስወግድ” የሚለውን ተጫን።

ስለ ተለዋዋጮች እና የአካላት ባህሪ የበለጠ መረጃ ለማግኘት የግሪንስቶን አደራጅ መመሪያ ምዕራፍ ሁለት ተመልከት።