5.7: በፊት የተሰጠ ሜታዳታ ማስገባት

ይህ ክፍል በፊት የተሰየመን ሜታዳታ እንዴት ማስገባት እንደሚቻል ይገልጻል፤ ወደ ክምችት ከመጨመራቸው በፊት ለሰነዶች የተሰጠ ሜታዳታ።

በላይብረሪያን በይነገጽ የታወቀ ሜታዳታ ቀድሞ ለፋይል የተሰጠ ከሆነ - ለምሳሌ ሰነዶችን ቀድሞ ካለ የግሪንስቶን ክምችት ስትመርጥ - ፋይሉን በምትጨምርበት ጊዜ ወዲያውኑ ይገባል። ይህንን ለማድረግ፣ ሜታዳታው በክምችት ውስጥ ካሉት የሜታዳታ ስብስብ ጋር ማፕ መደረግ አለበት።

ላይብረሪያን በይነገጽ አስፈላጊ መረጃዎችን ለመስጠት ይጠይቅዎታል። ጥያቄው ግልፅ መመሪያዎችን የሚሰጥ እና የገባውን ሜታዳታ ኢለመንት ስም ያሳያል፣ ልክ እንደ ምንጭ ፋይል ላይ እንደሚታየው። ይህን መስክ ኤዲት ማድረግ ወይም መለወጥ አይቻልም። ቀጥሎ አዲሱ ኤለመንት ከየትኛው ሜታዳታ ስብስብ ጋር ማፕ እንደሚደረግ ትመርጣለህ፣ እና ከዚያም ከዚያ ስብስብ ውስጥ ተገቢውን ሜታዳታ ኤለመንት ጥመርጣለህ። ሲስተሙ ወዲያውኑ ቅርብ የሆነ ዝምድና ያለውን፣ በስብስብ እና በኤለመንት፣ ለአዲሱ ሜታዳታ ይመርጣል።

የማፒንግ አሰራር ከተመርምሮ፣ ለተመረጠው ሜታዳታ ስብስብ አዲስ ሜታዳታ ኤለመንት ለመጨመር “አክል” የሚለውን ምረጥ። (ይህ ሊነቃ የሚችለው በተመረጠው ስብስብ ውስጥ ተመሳሳይ ስም ያለው ኤለመንት ከሌለ ብቻ ነው።) “አዋህድ” የሚለው አዲሱን ኤለመንት በተገልጋዩ ከተመረጠው ጋር ማፕ የደርገዋል። በመጨረሻም “ተወው” የሚለው በተመሳሳይ ስም የሚመጡ ሜታዳታዎችን አያስገባም። የተወሰነ ሜታዳታ እንዴት ማስገባት እንደሚቻል ካወቅህ የማፕ አሰራር መረጃው ለክምችቱ ከዚህ በኋላ እንደተቀመጠ ይቆያል።

ለዝርዝሩ ግሪንስቶን ሜታዳታ ለማጠራቀም የሚጠቀምበት የmetadata.xml ፋይሎች ዝርዝሩን፣ የግሪንስቶን አደራጅ መመሪያ ምዕራፍ 2 ተመልከት -- ከሰነድችህ ውስጥ ጥሩ ነገር ማግኘት እንድትችል ለማድረግ።