6.4: ኢንዴክሶችን ከፋፍፍ

ኢንዴክሶች የሚሰሩት በእንድ በተወሰነ ፅሁፍ ወይም ሜታዳታ ምንጮች ላይ ነው። ኢንዴክሶችን በመከፋፈል የፍለጋ ቦታን መቆጣጠር ይቻላል፣ በቋንቋ ወይም ቀድሞ በታወቀ ማጣሪያ መከፋፈል ይቻላል። ይህ ክፍል ይህ እንዴት እንደሚሰራ ምንሰራ ያብራራል። በ“ንደፍ” ትብ ስር “ኢንዴክሶች ከፍልፍል”ን ተጫን።

የ“ኢንዴክሶች ከፍልፍል” እይታ ሶስት ትቦች አሉት፣ “ማጣሪያዎችን መለየት”፣ “ክፍልፍሎችን መወሰን”፣ እና ”ቋንቋዎችን መወሰን” የሚሉት ናቸው። ስለ ክፍልፍሎች የበለጠ ለማወቅ ስል ንዑስ ክመችችቶች እና ንዑስ ኢንዴክሶች ከግሪንስቶን ፈበራኪው መመሪያ ምዕራፍ ሁለትን ተመልከት።

ለኤምጂ ክምችቶች ሊፈጠር የሚችልው ጠቅላላ የክፍልፍል ብዛት የሁሉም ኢንዴክሶች ጥምር፣ የንዑስ ክምችት ማጣሪያዎች እና የቋንቋዎች ምርጫ ድምር መሆኑን አስታውስ። ሁለት ኢንዴክሶች ከሁለት ንዑስ ክምችት ማጣሪያዎች በሁለት ቋንቋዎች ስምንት ኢንዴክስ ክፍልፍሎችን ይሰጡናል። ለኤምጂፒፒ፣ ሁሉም ኢንዴክሶች በአንድ ፊዚካል ኢንዴክስ የሚፈጠሩ ሲሆኑ፣ ሊኖረን የሚችለው አራት ኢንዴክስ ክፍልፍሎች ብቻ ናቸው። ለሉሲን፣ የፊዚካል ኢንዴክሶች ብዛት ለክምችቱ በተሰጠው ደረጃ የሚወሰን ይሆናል፡- ለአንድ ደረጃ አንድ ኢንዴክስ። ስለዚህ ከላይ ለተጠቀሰው ሁኔታ፣ አንድ ደረጃ አራት ኢንዴክሶች ሲኖሩት ሁለት ደረጃ ደግሞ ስምንት ኢንዴክሶች ይኖሩታል ማለት ነው።