6.2: የሰነድ ፕለጊኖች |
ይህ ክፍል የሰነዱ ፕለጊኖችን ለክምችት እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ይገልጻል። ፕለጊን እንዴተ መምረጥ ምን መጠቀም እናዳለብህ፣ ምን ግቤቶች ወደእነርሱ ማሳለፍ እንደሚቻል፣ እና በምን አይነት ቅደም ተከተል እንደተቀመጡ ያስረዳል። በ“ንድፍ” ትብ ስር “የሰነድ ፕለጊኖች” የሚለውን ተጫን።
ፕለጊን ለመጨመር፣ “ፕለጊን ለማስገባት ምረጥ” የሚለውን ታች አጠገቡ ካለው የዝርጋታ ዝርዝር ውስጥ በመምረጥ “ፕለጊን አስገባ” የሚለውን ተጫኑ። “ግቤቶችን በመውቀር ላይ" የሚል መስኮት ይመጣል። ለወደፊት የብራራል። እነዴ አዲስ ፕለጊን ከወቀርህ በኋላ “የተሰጡ ፕለጊኖች” መጨረሻ ላይ ይገባል። በአጠቃላይ እያንዳንዱ ፕለጊን አንድ አጋጣሚ ብቻ ይኖረዋል። ነገር ግን ተመሳሳይ ፕለጊኖች ከአንድ ጊዜ በላይ መጨመር ይቻላል። በዚህ ጊዜ ተደጋጋሚ አጋጣሚዎች ውጤታማ እንዲሆኑ በተለያየ ሁኔታ ይዋቀራሉ። (ለምሳሌ የprocess_exp ግቤት። http://wiki.greenstone.org/wiki/gsdoc/tutorial/en/enhanced_pdf.htm ተመልከት።
የፕለጊን አጭር ገላጣ ለመመልከት፣ ከ“ፕለጊን ለማስገባት ምረጥ” ዝርጋታ ዝርዝር ውስጥ ፕለጊኑን ምረጥ፣ ከዛም መዳፊቱን እዛው ላይ ማቆየት። መግለጫውን የሚያሳይ መርጃ ይቀርባል።
ፕለጊን ለማስወገድ፣ ፕለጊኑን ከዝርዝሩ በመምረጥ “ፕለጊን አስወግድ” ተጫን።
ፕለጊኖች የሚወቀሩት ግቤቶችን በመመገብ ነው።እነሱን ለመቀየር፣ ፕለጊኑን ከዝርዝሩ ምረጥና "ፕለጊን ወቅር" (ወይም ደብል-ክሊክ) ተጫን። ከዚያም “ግቤቶችን በመወቀር ላይ” የሚል መገናኛ የተለያዩ ግቤቶችን መቆጣጠሪያ ይዞ ይቀርባል።
የተለያዩ የመቂጣጠሪያ አይነቶች አሉ። አንዳንዶቹ ቼክ ቦክሶች ሲሆኑ አንዱን መጫን ለፕለጊን ተገቢውን አማራጭ ይጨምራል። ሌሎች ደግሞ የፅሁፍ ህብረቁምፊዎች ሲሆኑ ከቼክ ቦክስ ጋር እንዲሁም ከፅሁፍ ጋር ሊሆኑ ይችላሉ። ግቤቱን ለማንቃት ሳጥኑን ተጫን። ቀጥሎም ተገቢውን ፅሁፍ (ሬጉላር ኤክፕርሽን፣ የፋይለ ዱካ ወዘተ) በሳጥኑ ውስጥ ፃፍ። ሌሎች ደግሞ ከቀረቡ ዋጋዎች ውስጥ የሚመረጠ የሚመረጡ ዝርጋታ ማውጫዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ግቤት እንዴት እንደሚሰራ ለማወቅ መዳፊቱን ለተወሰነ ጊዜ በስሙ ላይ በማቆየት ወዲያው ገለጣ ይመጣል።
ውቅረቱን ስትቀይር “ይሁን” የሚለውን በመጫን ለውጦችን ማስረፅ እና መገናኛውን ዝጋ፣ ወይም “ሰርዝ” የሚለውን በመጫን ምንም ግቤት ሳይለወጥ መገናኛውን ዝጋ።
በዝርዝሩ ያሉ ፕለጊኖች በቅደም ተከተላቸው ይከወናሉ፣ ቅደም ተከተል ማስጠበቅ አልፎ አልፎ ጠቃሚ ነው። በዝርዝሩ ውስጥ ያለውን ፕለጊን በመምረጥ "Move Up" እና "Move Down" አዝራሮችን በመጠቀም ቦታውን ማቀያየር ይቻላል።