4.5: ፋይሎችን ዳግም መሰየም እና መተካት

ፋይሎችን ዳግም ለመሰየም ቀኛቸውን ጠቅ ማድረግ እና ከ "Rename" ዝርዝር ውስጥ መምረጥ። ከዛም አዲስ ስም ማስገባት እና “ይሁን”ን መጫን።

በክምችት ውስጥ ፋይሎች ለመተካት የፋይሉን ቀኙን ጠቅ አድርግ እና "Replace" መምረጥ። የፋይል ማሰሻ ይመጣል። አዲሱ ሰነድ አሮጌውን በክምችቱ ውስጥ ይተካዋል፣ እና ማንኛውም ሜታዳታ ወደዚህ ይሸጋገራል። ይህም በተለይ ተመሳሳይ ሰነዶችን (dummy documents) በትክክለኛዎቹ ለመተካት በጣም ጠቃሚ ነው።

አንዳንድ ፋይሎች በሶስተኛ ወገን ሶፍትዌር በሚገቡበት ጊዜ ወደ ኤችቲኤምኤል ይቀየራሉ፣ ለምሳሌ ወርድ፣ ኤክሴል፣ ፒዲኤፍ ወዘት ናቸው። በማስገባት ጊዜ የተፈጠረው ኤችቲኤምኤል በትክክል ፎርማት የተደረገ ላይሆን ይችላል። እነዚህ ሰነዶች በመዳፊት ተጨማሪ የቀኝ ክሊክ ምርጫ አላቸው፤ "Replace with HTML version"። ይህንን አማራጭ መምረጥ ዋናውን ፋይል በስብስብ ውስጥ የሚተካ እና ወደ ኤችቲኤምኤል የሚያዛውር ሲሆን በሌላ ጊዜ ኤዲት ማድረግ ይቻላል።