5.6: የተሰየሙ ሜታዳታዎችን መከለስ

አልፎ አልፎ ለተለያዩ ፋይሎች በአንድ ጊዜ የተሰጠ ሜታዳታ ማየት ትፈልግ ይሆናል-- ለምሳሌ፣ የቀሩት ፋይሎች ምን ይህል እንደሆኑ ለማወቅ፣ ወይም የቀኖችን ስርጭት እንዴት እንደሆነ ለማወቅ።

መመርመር የተፈለግከውን በክምችቱ ዛፍ ውስጥ ያሉ ፋይሎችን ምረጥ፣ በመቀጠልም ቀኙን ጠቅ በማድረግ “የተመደቡ ታዳታ…” የሚለውን ምረጥ። "ሁሉም ሜታዳታ" የሚል መስኮት በትልቅ ሰንጠረዥ ከብዙ አምዶች ጋር ይታያል። የመጀመሪያው አምድ የፋይሉን ስም ያሳያል፤ ረድፎቹ ደግሞ ለእነዚህ ፋይሎች የተሰጡ ሜታዳታ ዋጋዎችን ያሳያሉ።

ብዙ ፋይሎች ከተመረጡ ሰንጠረዡ መስራት ጥቂት ጊዜ ሊወስድ ይችላል። “ሁሉም ሜታዳታ” መስኮት ተከፍቶ እያለ የላይብረሪያን በይነገጽ መጠቀምህን መቀጠል ትችላለህ።

በጣም ትልቅ ሲሆን፣ “ሁሉም ሜታዳታ” ሰንጠረዥን አምዶቹ ላይ መጣሪያዎችን (filters) በመጠቀም ማጣራት ይቻላል። አዳዲስ መጣሪያዎች ሲጨመሩ፣ ተዛማጅ የሆኑ ረድፎች ብቻ ይታያሉ። ለመስራት፣ ለማስተካከል ወይም መጣሪያ ለማፅዳት፣ ከአምድ አናት ላይ ያለውን የ"ማጥለያ" አዶ ተጫን። ስለማጣሪው የሚገልፅ መረጃ ይመጣልሃል። መጣሪያው አንዴ ከተስተካከለ፣ የአምዱ ራስጌ ቀለም ይለወጣል።

የማጥሪያ ስንዱ “ቀላል“ እና “የረቀቀ" ትር አለው። ቀላሉ ስሪት አምዶችን ያጣራል፤ አምዶቹም የሚያሳዩት የተወሰነ ሜታዳታ ዋጋዎችን (“*” ሁሉንም የሚዛመድ) ብቻ የያዙ ረድፎችን ከተዘርጋፊ ዝርዝር በመምረጥ ይሆናል። የረቀቀው ስሪት የተለያዩ የማዛመጃ ስሌት መጠቀምን ያስችላል፤ መጀመር ያለበት፣ አያጠቃልልም፣ በፊደላዊ ያንሳል እና እኩል ይሆናል። የሚዛመደው ዋጋ አርታእ ሊደረግ የሚችል ማንኛውም ስትሪንግ (“*” ጨምሮ) ሲሆን፣ ማዛመዱ የሚፈለገውን መልከፊደል ይሁን አይሁን መምረጥ ይቻላል። በመጨረሻም፣ የተለያዩ ዋጋዎችን ለመግለፅ ሁለተኛ ማዛመጃ ሁኔታ መምረጥ (AND በመምረጥ) ወይም አማራጭ ዋጋዎችን ለማግኘት ደግሞ (OR በመምረጥ) መጠቀም ነው፡፡ ከዚህ በታች ያለው ቦታ ድርድር ቅደም ተከተሉን (ሽቅብታ ወይም ቁልቁልታ) ለመቀየር የሚያስችል ሳጥን ነው። አንዴ ይህን ካጠናቀክ፣ “ማጥሪያ አድርግ” በመጫን አዲሱ ማጥሪያ አምድ ላይ ተግብር። አሁን ያለውን ማጥሪያ ለማፅዳት “ማጣሪያ አጽዳ” ተጫን። ማሳሰቢያ ማጣሪያው ከተጣራ በኋላም የማጣሪያው መግለጫዎች ሊቀሩ ይችላሉ።

ለምሳሌ፡ የ“ሁሉም ሜታዳታ” ሰንጠረዥ ለመደርደር፣ አንድ አምድ ምረጥ፣ ነባሪውን የማጣሪያ ውቅረት ምረጥ (ቀላል ማጣሪያ በ “*” ላይ)፣ ከዚያም ሽቅብታ ወይም ቁልቁልታ ቅደም ተከተል ምረጥ።