2.2: ክምችቱን ማስቀመጥ |
ከ“ፋይል” አዶ ውስጥ “ጻፍ” በመምረጥ ስራውን ማስቀመጥ ይቻላል። አንድን ክምችት ማስቀመጥ በግሪንስቶን ውስጥ ለመጠቀም ማዘጋጀት ማለት አይደለም። (የራስህን ክምችት መፍጠር ተመልከት)።
የላይብረሪያን በይነገጽ የተሰራ ስራን ከፕሮግራሙ በመውጣት ወይም ሌላ ክምችት በመጫን ክምችቱ ዲስክ ላይ እንዲጻፍ በማድረግ ያግዛል።
ክምችቶች በግሪንስቶን መጫኛ አቃፊ “collect” የሚባል አቃፊ ውስጥ አጠር ባለ የክምችቱ ስም ይቀመጣል። የሚለውን በመስራት የሚቀመጡ ሲሆኑ አጭር የስብስብ ስም ይሰጣቸዋል፡፡ ሰነዶች "import" ንዑስ አቃፊ ውስጥ የሚጠራቀሙ ሲሆኑ ሜታዳታ የሚጠራቀመው በዚሁ አቃፊ "metadata.xml" ፋይል ውስጥ ይሆናል። የውቅረት መረጃ በ"etc" ንዑስ አቃፊ "collect.cfg" ፋይል ውስጥ ይቀመጣል። አንዳንድ መረጃዎች ለክምችቱ በተሰጠው ስም ፋይል ውስጥ በ".col" ቅጥያ ይቀመጣሉ።