6.3: ኢንዴክሶች ፈልግ |
ኢንዴክሶች የትኞቹ የክምችቱ አካላት እንደሚፈለጉ ይገልፃል። በዚህ ክፍል ኢንዴክሶችን እንዴት መጨመር እና ማጥፋት እንደሚቻል እና ነባሪ ኢንዴክስ እንዴት እንደሰጥ እንመለከታለን። ይህን ለማድረግ በ "Design" ስር ያለውን "Search Indexes" ተጫን።
የ"Search Indexes" ላይኛው ቀኝ በኩል የትኛው ኢንዴክስ በክምችት ውስጥ አገልግሎት ላይ እንደዋለ ያመለክታል። ይህንን ለመለወጥ "Change..." ተጫን። ብቅ ባይ መስኮት ከዝርዝር አማራጮች (ኤምጂ፣ ኤምጂፒፒ እና ሉሰን) ጋር ታያል። ይህንን መለወጥ በኢንዴክሶች ግንባታ ላይ ተጽእኖ የሚያሳድር ሲሆን የፍለጋ ተግባሩን ሊወይር ይችላል።
"Assigned Indexes" የሚለው ዝርዝር የትኞቹ ኢንዴክሶች ለክምችቱ እንደተሰጡ ያሳያል።
አንድን ኢንዴክስ ለመጨመር "New Index" ተጫን.... ይህን የሚያመለክት ብቅ ባይ መስኮት ከነዝርዝሩ በፅሁፍ እና በሜታዳታ ይቀርባል። የትኞቹን ምንጮች አባሪ ማድረግ እንደምትፈልግ ምረጥ። "Select All" እና "Select None" የሚሉት አዝራሮች ሁሉንም ዝርዝር ውስጥ ያሉትን ነገሮች ይመረምራሉ። አንዴ አዲስ ኢንዴክስ ከተሰየመ "Add Index" በመጫን ወደ ክምችት መጨመር ይቻላል። "Add Index" ይህ ለስራ ዝግጁ የሚሆነው መግለጫዎቹ አዲስ ኢንዴክስ ከሆኑ እና በክምችቱ ውስጥ የሌለ ከሆነ ነው።
ለኤምጂ ኢንዴክሶች፣ የኢንዴክሱን ግራኑላሪቲ ለመምረጥ ሲያስፈልግ "Indexing level:" ምናሌ ይጠቀሙ።
ለኤምጂፒፒ እና ሉሰን ኢንዴክሶች ግራኑላሪቲ በአለም አቀፍ ደረጃ እንጂ ለእያንዳንዱ ኢንዴክስ የተዘጋጅ አይደለም። ያሉት ደረጃዎች በዋናው "Search Indexes" ንጥል ላይ የተገለፁ ሲሆኑ የአመልካች ሳጥኖቹን በመምረጥ መጨመር ይቻላል።
ለኤምጂፒፒ እና ሉሰን ልዩ ኢንዴክስ ያለ ሲሆን “ሁሉም መስኮች” የሚለው ኢንዴክስ ለሁሉም ኢንዴክሶች ፍለጋ የሚሰራ እና ሁሉንም ምንጮች በተናጠል ለማግኘት የሚረዳ ነው። ይህንን ኢንዴክስ ለመጨመር "Add combined searching over all assigned indexes (allfields)" በመመርመር የምልክት ሳጥኖችን "Add Index" በመምረጥ ይሰራል።
ለኤምጂፒፒ እና ሉሰን ኢንዴክሶች "Add All" አዝራር የተዘጋጀ ሲሆን በዚህ ሁሉንም ሜታዳታ እና የፅሁፍ ምንጮች እንደ በተናጠል ኢንዴክሶች ለመጨመር ያስችላል።
አንድን ኢንዴክስ አርታእ ለማድረግ መምረጥ እና "Edit Index" መጫን። ከ "New Index" ጋር ተመሳሳይ መገናኛ ነው።
አንድን ኢንዴክስ ለማስወገድ፣ ካሉት ከተሰየሙት ኢንዴክሶች በመምረጥ "Remove Index"ተጫን።
ኢንዴክሶች በተሰየሙ ኢንዴክሶች ውስጥ የተቀመጡበት ቅደም ተከተል በፍለጋ ገፅ ላይ በተቆልቋይ ምናሌ ውስጥ ባላቸው አቀማመጥ መሰረት ነው። "Move Up" እና "Move Down" አዝራሮችን በመጠቀም ቅደም ተከተላቸውን መቀየር ይቻላል።
በነባሪ የተመረጠው የፍለጋ ገጽ “ነባሪ ኢንዴክስ” ተብሎ ይጠራል። ይህም ኢንዴክሱን ከዝርዝር ውስጥ በመምረጥ የሚሰጥ ሲሆን ይህን ለማድረግ “ነባሪ አድርግ” የሚለውን ተጫን። ነባሪ ኢንዴክስ “[ነባሪ ኢንዴክስ]” በሚል መለያ በ”የተሰጡ ኢንዴክሶች” ዝርዝር ውስጥ ይገኛል። ነባሪ ኢንዴክስ ካልተሰጠ፣ በዝርዝሩ ውስጥ ካሉት የመጀመሪያው ነባሪ ኢንዴክስ ሆኖ ያገለግላል።
በፍለጋ ገፁ ላይ ለተዘርጋፊ ዝርዝር ኢንዴክሶች የሚያገለግሉ ስሞች በ "Search" ውስጥ በ"Format" ውስን ቦታ ውስጥ መስጠት ይቻለላል። ለበለጠ መረጃ ተመልከት።