5.2: የሜታዳታ ስብስቦችን መምረጥ |
ቀድሞ የተሰየሙ ሜታዳታ ኤለመንቶች ስብስብ “ሜታዳታ ስብስብ" በመባል ይታወቃል። ለዚህ ምሳሌ የሚሆነው ዱብሊን ኮር ሜታዳታ ስብስብ ነው። ወደ ክምችትህ የሜታዳታ ስብስብ በምታክል ጊዜ ኤለመንቶቹ ለመምረጥ ዝግጁ ይሆናሉ። ከአንድ በላይ ስብስብ ሊኖር የሚችል ሲሆን የስም መጣረስን ለማስቀረት አጭር መለያ በኤለመንቱ ስም ላይ ይጨመራል። ለምሳሌ ዱብሊን ኮር ኤለመንት Creator የሚለውን "dc.Creator" ይሆናል። ሜታዳታ ስብስቦች በላይብረሪያን በይነገጽ ሜታዳታ አቃፊ ውስጥ የሚጠራቀሙ ሲሆኑ ድህረቅጥያቸውም ".mds" ይሆናል።
አዲስ ክምችት ስትፈጥር ዱብሊን ኮር ሜታዳታ ስብስብ በነባሪ ይጨመራል። "Manage Metadata Sets..." በመጫን የሚፈለገውን ሜታዳታ ስብስብ ለማዘጋጀት በስብስቡ ዛፍ በታች ያለውን የማበልፀግ እይታ መጠቀም ነው። ይህን አዲስ መስኮት በማምጣት የክምችቱን ሜታዳታ ስብስብ ለመቆጣጠር አመቺ ይሆናል።
የ "Assigned Metadata Sets" ዝርዝር የሚያሳይህ በክምችቱ ምን ስብስቦች አሁን እየተጠቀምክ መሆንህን።
ከተጫነው ክምችት ጋር ሌላ ሜታዳታ ስብስብ ለመጠቀም “አክል…” ተጫን። ከዚያም ጂኤልአይ የሚያውቀው ነባሪ ሜታዳታ ስብስቦች በብቅ ባይ መስኮት ይታያል። ከእነዚህ ውስጥ አንዱን ለመጨመር ከዝርዝሩ ውስጥ በመምረጥ “አክል” የሚለውን ተጫን። የራስህን ሜታዳታ ሰይመህ ከሆነ “አስስ” ቁልፍን በመጠቀም ፋይሉን ጠቁሞ ማስገባት ይቻላል።
አዲስ ሜታዳታ ስብስብ ለመፍጠር “አዲስ…” ተጫን። ይህ የግሪንስቶን የሜታዳታ ስብስቦች ኤዲተር ጂኢኤምኤስ እንዲነሳ ያደርጋል። በቅድሚያ በብቅ ባይ መስኮት የስብስቡ ስም፣ የስምቦታ እና መግለጫ እንድትሞላ ይጠይቃል። እንዲሁም አዲሱን ስብስብ ባለው ላይ ለመመስረት መምረጥ የሚቻል ሲሆን በዚህ ጊዜ ሁሉንም ኤለመንቶች ከተጠቀሰው ስብስብ ውስጥ እንዲወርስ ያደርጋል። ከዛም “ይሁን”ን ተጫን። ዋናው መስኮት የሜታዳታ ስብስብ ኤለመንቶችን በግራ በኩል የሚያሳይ ሲሆን ለስብስቡ የሚሆኑት ባህሪያት በቀኝ በኩል ይቀመጣሉ። ስብስቡን ቀደም ሲል ባለው ላይ መስርተህ ከሆነ አንድ ወይም ከዚያ በላይ ኤለመንቶች ይታያሉ። አንዱን መጫን በቀኝ በኩል ያለውን ባህሪ ያሳያል፡፡
አዲስ ኤለመንት ለመጨመር የስብስቡን ቀኙን ጠቅ ማድረግ "ኤለመነት አክል"ን ምረጥ። አዲስ ንዑስ ኤለመንት ለማከል የስብስቡን ቀኙን ጠቅ በማድረግ "ንዑስ ኤለመንት አክል" የሚለውን ምረጥ። ኤለመንቶች እና ንዑስ ኤለመንቶች ለመሰረዝ “ኤለመንት ሰርዝ” ወይም "ንዑስ ኤለመንት ሰርዝ" ከቀኙን ጠቅ ምናሌ ምረጥ።
ማሳሰቢያ፤ የግሪንስቶን የሜታዳታ ስብስቦች ኤዲተር ከጂኤልአይ ውጭ በተናጠል መስራት ሚችል ሲሆን ከግሪንስቶን አቃፊ ከጀምር ምናሌ (Start menu) ውስጥ መምረጥ ነው፣ ወይም ከግሪንስቶን ጭነት አቃፊ ውስጥ የ gems.sh ወይም gems.bat ፋይልን ማስነሳት።
አልፎ አልፎ ሁለት ሜታዳታ ስብስቦች ተመሳሳይ የስምቦታ ሊኖራቸው ይችላል፣ ለምሳሌ ዱብሊን ኮል እና ኳሊፋይድ ዱብሊን ኮር ሁለቱም የሚጠቀሙት የስያሜቦታ “ዲሲ” ነው። እነዚህን ስብስቦች በክምችት ውስጥ በተመሳሳይ ጊዜ መጠቀም አይቻልም። በክምችት ውስጥ በአገልግሎት ላይ የዋለ የስያሜቦታ መጠቀም ከሞከርህ ማስጠንቀቂያ ይቀርብልሃል። በዚህ ከቀጠልህ ያለው ስብስብ ተሰርዞ አዲሱ ይተካል። ማንኛውም የተሰጠ ሜታዳታ ዋጋ ወደ አዲሱ ስብስብ ተሸጋግሮ እነዚህ ኤለመንቶች ይቀመጣሉ።
ጂኢኤምኤስ በመጠቀም ያለውን የሜታዳታ ስብስቦችን አርታእ ማድረግ እና አዳዲሶችን መፈጠር ይቻላል። “አርታእ” የሚለውን ቁልፍ በመጫን ያሉትን ሜታዳታዎች መክፈት ይቻላል። አንዴ አርታእ ማድረጉን ካጠናቀቁ (ከላይ እንደተገለፀው) አስቀምጠው (ፋይል - አስቀምጥ) እና ጂኢኤምኤስን ዝጋ።
አንድ ክምችት የሜታዳታ ስብስብ የማያስፈልገው ከሆነ፣ ምረጠውና “አስወግድ” የሚለውን ተጫን። ለኤለመንቶች ሜታዳታ ሰይመው ከሆነ በሚቀጥለው ጊዜ ክምችቱን ሲከፈት ምን ማድረግ እንደምትችል ይጠይቅሃል።