5.1: የማበልፀግ እይታ

በክምችቱ ውስጥ ላሉት ሰነዶች ሜታዳታ ለመሰየም "Enrich" ተጠቀም። ሜታዳታ ማለት ስለአንድ መረጃ የሚገልፅ መረጃ ሲሆን በተለይ ርዕስ፣ ፀሐፊ፣ የተሰራበት ቀን የመሳሰሉትን የሚገልፅ ነው። ሜታዳታ እያንዳንዱ ሁለት አካል አለው። "Element" ምን አይነት ዓይነት እንደሆነ (ለምሳሌ ፀሐፊው)፣ እና "Value" የሚለው ደግሞ የሜታዳታው ኤለመንት ዋጋ (ለምሳሌ የፀሐፊው ስም) ይሰጠናል።

ከ "Enrich" ዕይታ በስተግራ ያለው የክምችቱ ዛፍ ነው። ሁሉም ቀኙን ጠቅ አሰራሮች በ"Gather" ክምችት ዛፍ ዕይታ ውስጥ የሚገኝው ሁሉ በዚህም ይገኛል። በቀኝ በኩል የሚታየው የሜታዳታ ሰንጠረዥ የሚያሳየው በክምችት ዛፍ ውስጥ የሚገኝ ማንኛውንም የተመረጠ ፋይል ወይም አቃፊ ነው። ኮለኖች በጥቁር ከላይኛው ገፅ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ የመለያ መስመሩን በመጎተት መጠኑን ማስተካከል ይቻላል። የተመረጡት ብዙ ፋይሎች ወይም አቃፊዎች ከሆኑ፣ ጥቁር ፅሁፍ የሚያሳየው ዋጋው ለተመረጡት ሁሉ ተመሳሳይ መሆኑን እና ግራጫ ቀለም ተመሳሳይ አለመሆኑን ነው። ግራጫ ዋጋዎችን መቀየር እዚያ ሜታዳታ ውስጥ ያሉትን ብቻ የሚለውጥ ነው። ማንኛውም አዲስ የገባ ሜታዳታ ወጋዎች ለተመረጡት ሁሉ ያገለግላል።

ለተወሰኑ ሜታዳታ ምዝግቦች የአቃፊ አዶ ሊታይ ይችላል። ይህም ዋጋዎቹ ከወላጅ ወይም ከዘር ግንድ አቃፊ የተወረሱ መሆናቸውን ያሳያል። ከዘር የተወረሱ ሜታዳታዎች ማስተካከልም ማስወገድም አይቻልም። ወደ ሜታዳታ የተሰየመለት አቃፊ በቀጥታ ለመሄድ የአቃፊውን አዶ መጫን ነው።

በሰንጠረዡ ውስጥ ያለውን ሜታዳታ መጫን ያሉትን የዚያን ኤለመንት ዋጋዎች የሚያሳይ ሲሆን "Existing values for ..." ደግሞ ከሰንጠረዙ በታች ይታያል፡፡ ይህ “ትሪ ቫሊዩ” ማራዘም እና ማሳጠር ይቻላል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ለተመረጠው ኤለመንት የበፊት ዋጋ የሚያሳይ ነው፡፡ አንድን ኢንትሪ ወዲያውኑ መጫን የዋጋ ፊልድ ውስጥ ያስገባዋል፡፡ በተቃራኒው በዋጋ ፊልድ ውስጥ መፃፍ የዛፍ ዋጋ ኢንትሪ በመምረጥ የፃፉት ፊደል ይጀምራል፡፡ በዚህ ጊዜ ታብ የሚለውን በተን መጫን የጽሀፉ ስራውን በተመረጠው ዋጋ እንዲጠናቀቅ ያደርገዋል፡፡

የሜታዳታ ዋጋዎች በተዋረድ ማጠናቀር ይቻላል። ይህም በዛፍ ዋጋ ውስጥ በውስጥ ደረጃ አቃፊዎችን በመጠቀም ሊታይ ይችላል። እነዚህ ተዋረዳዊ ዋጋዎች "|" ሕብረቁምፊ በመጠቀም ደረጃዎችን መለያየት ይቻላል። ለምሳሌ “ኢትዮጵያIኦሮሚያIገለምሶ” አገርን ቅደም ተከተል መወከል ይችላል። ይህም ዋጋዎችን ለመከፋፈል ይረዳል። ይህ ወጋዎችን እንድ ላየ ለመቦደን ያስችላል። ቡድኖች እንደ ሜታዳታ ለፋይሎች ሊሰጡ ይችላል።

ግሪንስቶን ከሰነዶች ሜታዳታዎችን በራስ ፈልጎ የሚያወጣ ሲሆን የእነዚህ ኤለመንቶች የፊት ቅጥያ "ex.” ነው። ይህ የዛፍ ዋጋ የሌለው እና ሊስተካከል የማይችል ነው።