8.1: የቅርጽ እይታ

በዚህ ክፍል ስለ ቅርጽ እይታ እንመለከታለን።

በላይብረሪያን በይነገጽ ክምችት ለተጠቃሚው እንዴት መታየት እንዳለበት መወቀር ትችላለህ። የመወቀሪያ አማራጮች በክፍል በክፍል የተመደቡ ሲሆኑ እያንዳንዱ የራሱ የሆነ ማስተካከያ አለው።

በግራ በኩል የግቤት ዝርዝር ሲኖር በቀኝ በኩል ለእያንዳንዱ ግቤት መቆጣጠሪያ ተቀምጧል። አንድን ግቤት ለመለወጥ በዝርዝሩ ውስጥ ስሙን ተጫን።

በግቤቶች ዝርዝር ስር "ክምችት ቅድመ ዕይታ" አዝራር አለ። በቅርፀት ዕይታ የተደረገ ለውጥ የክምችት ዳግም ግንባታ አይፈልግም። ይሁንና፣ ቅድመ ዕይታን ለማስቻል ክምችቱ ቢያንስ አንድ ጊዜ መገንባት አለበት።