3.1: የአውርድ እይታ

በዚህ ክፍል ውስጥ የማውረድ ስራ እንዴት እንደምናስታካከል እና እንዴት እንደምንቆጣጠር እናያለን። "Download" የሚለውን ትብ በመጫን እይታውን መክፈት ከዚያም የስክሪኑ የላይኛው ግማሽ አካል የአውርድ መቆጣጠሪያዎችን ያመጣል። የታችኛው ግማሽ ክፍል በመጀመሪያ ባዶ ይሆንና ወደ ስራ ሲገባ ያለቁ እና ስራ ላይ ያሉትን የማውረድ ስራዎችን ያሳያል።

ምዝግቦችን ለማውረድ የሚረዱ ብዙ ፕሮቶኮሎች ሲኖሩ፣ እነዚህም በግራ በኩል ከአናት ላይ ተዘርዝረው ይታያሉ።

ድር፤ ኤችቲቲፒ እና ኤፍቲፒ በመጠቀም የድረ ገፆችን እና ፋይሎችን አውርድ።

ሚዲያዊኪ፤ ኤችቲቲፒ በመጠቀም ድረ ገፆችን እና ፋይሎችን ከሚዲያዊኪ ድህረገፅ አውርድ።

OAI፤ የሜታዳታ ምዝግቦችን ከኦኤአይ-ፒኤምኤች (ኦፕን አርካየቭ ኢኒሺዬቲቭ) አገልጋይ ላይ አውርድ።

ዜድ39.50፤ የማርክ (MARC) ምዝግቦችን የተወሰነ የፍለጋ መስፈርትን የሚያሟሉትን ከዜድ39.50 አገልጋይ ላይ አውርድ።

SRW፤ የማርክ ኤክስኤምኤል (MARCXML) ምዝግቦችን የተወሰነ የፍለጋ መስፈርትን የሚያሟሉትን ከኤስአርደብሊው አገልጋይ አውርድ።

ተገቢውን ፕሮቶኮል በግራ በኩል ካለው ዝርዝር ውስጥ ምረጥ። በቀኝ በኩል ያለው ደግሞ ለተመረጠው የማውረጃ ፕሮቶኮሎች ያሉትን አማራጮች ያሳያል። አማራጩ ምን እንደሚሰራ ለማግኘት መዳፊቷን እላዩ ላይ ማቆየት ከዚያም አማራጩን የሚገልፅ አስረጅ ይቀርባል። አንዳንድ አማራጮች “አማራጭ” ናቸው፤ እነዚህ የሚቀርቡት ከማመልከቻ ሳጥን ጋር ስለሆነ አማራጩን ለመጠቀም መምረጥ (ቲክ ማድረግ) ያስፈልጋል። ሌሎች “የግድ” የሚሉ የማመልከቻ ሳጥን የሌላቸው ፣ እና የማውረድ ስራ ከመጀመሩ በፊት ዋጋ የሚያስፈልጋቸው ናቸው።

አንዴ ውቀራው ከተስተካከለ በኋላ "Server Information" በመጫን ከአገልጋዩ ጋር የተገናኘ መሆኑን ለማረጋገጥ እና ስለድረ ገፁ ወይም ስለ አገልጋዩ መሰረታዊ መረጃዎችን ለማየት፤ ወይም "Download" በመጫን ማውረድ ማስጀመር ይቻላል።

ተጨማሪ ሁለት አዝራሮች አሉ "Configure Proxy..." በምርጫዎች ምናሌ ውስጠ የዕጅ አዙር ቅንብር ወደ ሚስተካከልበት የግንኙነት ክፍልን፣ እና "Clear Cache" በፊት የወረዱ ፋይልችን ለመሰረዝ ወደ ሚያስችል ያገናኛል። የዕጅ አዙር መረጃዎችን በማስተካከል የዕጅ አዙርን አገልጋይ ኢንተርኔትን እንዲገናኝ ማድረግ ይቻላል። ማረጋገጫ ካስፈለገ በማውረድ ሂደት ውስጥ የዕጅ አዙር አገልጋዩ የተገልጋይ ስም እና የይለፍ ቃል ይጠይቃል። የላይብረሪያን በይነገጽ የይለፍ ቃሉን ለተለያዩ ክፍለ ጊዜያት ይዞ አይቆይም።

ፋይሎች ሲወርዱ የሚቀመጡት በ "Downloaded Files" አቃፊ ውስጥ ነው (ይህ የሚሆነው ፋይል ማውረድ ሲነቃ ብቻ ነው)፣ እና በማንኛውም ክምችት መጠቀም ይቻላል። ፋይሎች የሚሰየሙት ከወረዱበት ዩአርኤል (ለዌብ እና ሜዲያዊኪ) ስም ነው ወይም የዩአርኤል እና ተጨማሪ ዋጋዎች (ለሌሎች ዳውንሎድ አይነቶች) ነው። አዲስ አቃፊ ለእያንዳንዱ የሚከፈት ሲሆን ሌሎቹ ይህንን ተከትለው የወርዳሉ። ይህም እያንዳንዱ ፋይል የተለያየ መሆኑን ያረጋግጣል።

የዳውንሎድ ዝርዝር ለእያንዳንዱ የዳውንሎድ ሂደት ምዝግብ አለው። እያንዳንዱ ምዝግብ የመጻፊያ ቦታ ያለው ሲሆን የስራውን ዝርዝር ለመፃፍ እና አሁን እየተሰራ ያለው ስራ ሂደቱ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ያሳያል። በእያንዳንዱ ምዝግብ ወይም ኢንትሪ ሶስት ቁልፎች ይታያሉ። ከእነዚህም "Pause" አንድን ስራ ባለበት ለማቆም ይጠቅማል። "View Log" ደግሞ የዳውንሎድ ልግ ፋይልን መስኮት በመክፈት ያሳያል። "Close" ፋይል ማውረድ እንዲቋረት እና ስራው እንዲወገድ ያደርጋል።