8.5: ፅሁፍ ተርጉም

በዚህ ክፍል የትርጉም ንጥልን የሚገለፅ ሲሆን አንድን ክምችት በይነገጽ ወደ ሌላ ቋንቋ ለመተርጎም ያስችላል። ከ“ቅርጽ” ትብ ስር “ፅሁፍ ተርጉም” የሚለውን ተጫን።

በመጀመሪያ ከ”ባህሪ” ዝርዝር ውስጥ ምዝግብ ምረጥ። በቋንቋ-የተወሰኑ ሕብረቁምፊዎች ጋር ተያያዥ ባህሪ የታያል። ከዚያም "የሚተረጎምበት ቋንቋ" ጸዘርጋፊ ዝርዝር ውስጥ የሚፈለገውን ቋንቋ በመምረጥ የተተረጎመውን ጽሁፍ ወደ ጽሁፍ ቦታ በማምጣት አስፈላጊ ከሆነ ለመመልከት ወደ “የመነሻ ጽሁፍ” በማምጣት ማየት ይቻላል። ስትጨርስ “ትርጉም አክል” የሚለውን ተጫን።

ያለውን ትርጉም ለማስወገድ “የተሰየሙ ትርጉሞች” የሚለውን ሰንጠረዥ በመምረጥ “ትርጉም አስወግድ” የሚለውን ተጫን።

ትርጉምን ለማአርታእ፣ የሚተረጎመውን መርጠህ፣ “የተተሮጎመ ጽሁፍ”ን አርታእ እና “ትርጉም ተካ” የሚለውን ቁልፍ ተጫን።