5.5: ሜታዳታ ማስተካከል ማድረግ ወይም ማስወገድ

አንድን ሜታዳታ ለማስተካከል ወይም ለማስወገድ፣ በመጀመሪያ ተፈላጊውን ፋይል ምረጥ፣ ከዚያም ከሰንጠረዡ ውስጥ የሜታዳታ ዋጋ ምረጥ። የዋጋ መስኩን አስተካክል፣ ካስፈለገ ሜታዳታን ለማስወገድ ሁሉንም ጽሁፎች ሰርዝ።

ነዑስ አቃፊ ወይም ከአንድ በላይ ፋይሎች የያዘ አቃፊ ለመዘመን ሂደቱ ተመሳሳይ ነው፣ ነገር ግን መዘመን የሚቻለው ለሁሉም ፋይሎች/አቃፊዎች መምረጥ የሚቻለውን ሜታዳታ ብቻ ነው።

የዋጋ ዛፍ ለአሁን ክፍለጊዜ በቅርቡ የተሰጡትን ዋጋዎች እና አሁኑ የተሰጡትን ዋጋዎች የሚያሳይ ነው፣ ስለሆነም የተለወጡ ወይም የተሰረዙ ዋጋዎች በዛፉ ላይ ይቀራሉ። ክምችቱን መዝጋት እና እንደገና መክፈት የማያስፈልጉትን ሁሉንም ዋጋዎች ያስወግዳል።