8.6: ክምችት ዘለል ፍለጋ |
ግሪንስቶን የተለያዩ ብዙ ክምችቶችን እንደ አንድ ለመፈለግ ያስችላል። ይህም ሌሎች ክምችቶችን አሁን ካለው ክምችት ጋር በመሰየም የሚሰራ ነው። ከ“ቅርጸት” ትብ ስር “ክምችት ዘለል ፍለጋ” የሚለውን ተጫን።
የክምችት ዘለል ፍለጋ ፓኔል ያሉትን ክምችቶች በዝርዝር ያስቀምጣል። አሁን ያለው ክምችት ምልክት የተደረገበት ስለሆነ አለምመረጥ አይቻልም። ሌላ ክምችት በፓነል ውስጥ አብሮ ለመፈለግ በዝርዘሩ ውስጥ ስሙን ምረጥ (ለማጥፋት እንደገና ተጫን)። የተመረጠው አንድ ክምችት ብቻ ከሆነ ክምችት ዘለል ፍለጋ ማካሄድ አይቻልም።
የተናጥል ክምችቶች ተመሳሳይ ኢንዴክሶች ከሌላቸው (ንዑስ ክምችት ክፍልፋዮች እና የቋንቋ ክፍልፋዮችን አጠቃሎ) የክምችት ዘለል ፍለጋ በትክክል አይሰራም። ተጠቃሚው ለሁሉም የክምችት ፍለጋ የጋራ ኢንዴክስ መጠቀም አለበት።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፣ የግሪንስቶን አደራጅ መምሪያ ምዕራፍ አንድ ተመልከት።