4.4: ፋይሎችን መጨመር

ፋይሎች ጎትቶ እና በመውርወር ወደ ክምችቱ መቅዳት ይቻላል።የመዳፊቷ ጠቋሚ የተመረጠው ፋይል ተሸካሚ (ወይም ከአንድ በላይ ከተመረጠ ብዛታቸው) ይሆናል። ፋይሎቹን ለመቅዳት የተመረጠውን ወደ ክምችቱ ዛፍ ጣለው ወይም በክምችቱ ውስጥ ወዲህ ወዲያ በማንቀሳቀስ ...

ከእንድ በላይ ፋይሎች ሲቀዱ፣ ሁሉም በተመሳሳይ ደረጃ በተፈለገው አቃፊ ውስጥ ያለምንም የአቃፊ መዋቅር እና አፈጣጠር እንዲቀመጡ ይደረጋል። በአንድ አቃፊ ውስጥ ተመሳሳይ ስም ያለው ሁለተኛ ፋይል ሲቀዳ የመጀመሪያውን ፋይል ለመደረብ የፈለግህ አንደሆነ ይጠይቃሃል። በዚህ ጊዜ “ተው” የሚለውን በመምረጥ ፋይሉ ሳይቀዳ ይቀርና ሌሎች የተለየ ስም ያላቸው ፋይሎች እንዲቀዱ ይሆናል። ሌሎች የቅጂ ትእዛዞችን ለመሰረዝ “አቁም” ቁልፍን ተጫን።

በተመረጠው ውስጥ “ከፍተኛ” የሆኑ ዓይነቶች ብቻ ይዛወራሉ። አንድ አቃፊ ከልጆቹ የበለጠ ነው። በአንድ አቃፊ ውስጥ ፋይሎችን እንዲሁም ራሱ አቃፊውን መምረጥ አይቻልም።

አንድን ፋይል ስታክል፣ የላይብረሪያን በይነገጽ በምንጭ አቃፊዎች ለምታክለው ፋይል ቀድሞ የተሰየመ ሜታዳታ የያዙ ተጨማሪ ፋይሎችን (auxiliary files) ፍለጋ ይጀምራ፣ አንዱ ከተገኘ ይህንን ሜታዳታ ማስገባት ይጀምራል። በሂደቱ ላይ እያለ፣ ተጨማሪ መረጃ በመስጠት ለገባው ሜታዳታ የክምችት መረጃ በተደጋጋሚ ሊጠይቅ ይችላል። ይህ ሂደት የተለያዩ ማሳሰቢያዎችን የያዘ ሲሆን በሚከተለው መግለጫ ተመልከት፡ በፊት የተሰጠ ሜታዳታ ማስገባት።ሜታዳታ ከፋይሎች ጋር የማዛመድ ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለግህ የግሪንስቶን አደራጅ መመሪያ- Getting the most out of your documents ምዕራፍ ሁለትን ይመልከቱ።

እንዲሁም በስብስቡ የቀኝ ማውስ በመጫን “ዱሚ” ሰነዶችን መጨመር ወይም በፎልደር ላይ መጨመር የሚቻል ነው፡፡ ይህም የሚከተለውን በመምረጥ ይሆናል፡፡ "New dummy document" ይህ ሜታዳታ የሚሰጥበት አዲስ ፋይል ይከፍታል፡፡ በሌላ ጊዜ ፋይሉ በትክክለኛ “ሪል” ፋይል ሊተካ ይችላል፡፡