5.3: አዲስ ሜታዳታ መጨመር

አሁን ሜታዳታ ዓይነት ለፋይል እንጨምራለን--ኤለመንት እና ዋጋ። በመጀመሪያ ከክምችቱ ፋይል ዛፍ በግራ በኩል ፋይሉን ምረት። በዚህ ተግባር በፊት ለዚህ ፋይል የተሰየመ ሜታዳታ በሰንጠረዙ በቀኝ በኩል እንዲታይ ያደርጋል።

በመቀጠል መጨመር የፈለግከውን ሜታዳታ ኤለመንት የሰንጠረዡን ረድፍ በመጫን ጨምር።

ከዚያ ዋጋውን የዋጋ መስኩ ላይ ፃፍ። በ የማበልፀግ እይታ እንደተጠቀሰው፣ መዋቅሩ ለመጨመር “I” ምልክት ተጠቀም። [ወደላይ] ወይም [ወደታች] ማመልከቻ ቁልፎችን በመጫን ሜታዳታ ዋጋው እንዲቀመጥ እና ምርጫው በተገቢው እንዲሄድ ያደርጋል። የ[አስገባ] ቁልፍ በመጫን ሜታዳታውን ለማስቀመጥ እና አዲስ ባዶ ምዝግብ ለሜታዳታ ኤለመንት ለመፍጠር፣ እነዲሁም ከአንድ በላይ ዋጋዎችን ለሜታዳታ ኤለመንት ለመስጠት ያስችላል።

በተጨማሪ ሜታዳታ ወደ አቃፊ መጨመር፣ ወይም ለብዙ ፋይሎች አንድ ጊዜ መጨመር ይቻላል። በአቃፊ ውስጥ ባሉ ሁሉም ፋይሎች ላይ ወይመ በተመረጡት ላይ በአንዴ ይጨመራል፣ ለንዑስ አቃፊዎችም እንዲሁ። ማንኛውም በአቃፊው ውስጥ የሚፈጠር አዲስ ፋይል የአቃፊውን ዋጋ በራሱ ይወርሳል።