6.4.3: ቋንቋዎችን ስጥ |
በዚህ ክፍል የፍለጋ ኢንዴክሶችን እንዴት ለተለየ ቋንቋ መወሰን እንደሚቻል በዝርዝር እንመለከታለን።ይህንን ለመስራት ከ"ኢንዴክሶችን ከፋፍል" ውስን ቦታ ላይ “ቋንቋዎችን ስጥ” ትብ በመጠቀም ክፍልፋይ በመፍጠር ነው።
የቋንቋ ክፍልፋዮች የትኞቹ ሰነዶች በተሰየሙ ቋንቋዎች እንደተገለፁ እና በክፍልፋዩ ውስጥ እንደሚገቡ ሜታዳታ ይጠቀማሉ። ግሪንስቶን ለአብዛኞቹ ሰነዶች "ex.Language" የሚባል ሜታዳታ ሲሆኑ ይህም ነባሪ የሜታዳታ አጠቃቀም ነው። ነገር ግን ይህ ለማስተካከል "Language Metadata:" በመጠቀም ትክክለናውን ሜታዳታ ነገር ማስገባትይቻላል።
አዲስ የቋንቋ ክፍልፋይ ለማከል "ቋንቋዎች ለማከል” ከሚለው ዝርዝር ውስጥ አንድ ወይም ከዚያ በላይ ቋንቋዎችን በመምረጥ "ክፍልፋይ አክል” ሚለውን ተጫን።
ያለውን ክፍልፋይ ለመለወጥ ከ”የተሰጡ የቋንቋ ክፍልፋዮች” ዝርዝር ውስጥ ምረጥ፣ ከታች ባለው የ"ቋንቋዎች ለማከል" ዝርዝር ውስጥ ቋንቋውን አስተካክል፣ እና “ክፍልፋይ ተካ” የሚለውን ተጫን።
አንድን የቋንቋ ክፍልፋይ ለማስወገድ፣ ከ”የተሰጡ የቋንቋ ክፍልፋዮች” ዝርዝር ውስጥ በመምረጥ “ክፍከፍል አስወግድ” የሚለውን ተጫን።
የቋንቋ ክፍልፍሎቹ በተሰጣቸው ቅደም ተከተል የተሰየሙ መሆናቸው ምክኒያት በመፈለጊያ ገፅ ላይ በተቆልቋይ ውስጥ በቅደም ተከተል መታየታቸው ነው።ይህንን ቅደም ተከተል ለመለወጥ "Move Up" እና "Move Down" ቁልፎችን ይጠቀሙ።
ነባሪ የቋንቋ ክፍልፋይ ለማዘጋጀት፣ ከዝርዝሩ ውስጥ በመምረጥ “ነባሪ አዘጋጅ” የሚለውን ተጫን።
በፍለጋ ገፁ ላይ ለተቆልቋይ ዝርዝር የቋንቋ ክፍለፍሎች የተጠቀምናቸው ስሞችን "Search" ውስጥ በ"Format" ውስን ቦታ (ፍለጋ ተመልከት) ላይ ማስተካከል ይቻላል።