6.5: የማሰሻ ከላሲፋየሮች

ይህ ክፍል እንዴት “ክላሲፋየሮችን” ተጠቅመን በክምችት ውስጥ ማሰስ እንደምንችል ያስረዳናል። “ንድፍ” በሚለው ትብ ስር “የማሰሻ ከላሲፋየሮች” የሚለውን ተጫን።

አንድ ክላሲፋየር ለመጨመር “ክላሲፋየር ለማከል ምረጥ” የሚለውን ተቆልቋይ ዝርዝሩ በመምረጥ ከዚያ “ክላሲፋየር አክል…” የሚለውን ተጫን። እንዲህ የሚል መስኮት ይከፈታል “ግቤቶችን መወቀር”፤ ለዚህ ዳያሎግ የተሰጡ መመሪያዎች ለፕለጊን ከተሰጡት ጋር ተመሳሳይ ናቸው። (የሰነድ ፕለጊኖች ተመልከት)። አንዴ አዲስ ክላሲፋየር ካስተካከልህ በኋላ “የተሰየሙ ክላሲፋየሮች” በሚለው ዝርዝር መጨረሻ ላይ ተጨምሮ ታገኘዋለህ።

የአንድን ክላሲፋየር አጭር መግለጫ ለመመልከት “ክላሲፋየር ለማከል ምረጥ” በሚለው ዝርዝር ወደታች በመሄድ መዳፊቱን ላዩ ላይ ማቆየት። ይህን መግለጫ የሚሰጥ የምክር መርጃ ወዲያውኑ ይታያል።

እያንዳንዱ ክላሲፋየር የሚስተካከሉ ብዙ ግቤቶች አሉት። ጠቃሚ ግቤቶች “ሜታዳታ” የያዙ ሲሆኑ ይህም ሰነዶች የሚመደቡበት ሜታዳታ የሚገልፅ እና “የቁልፍስም” የሚለው ደግሞ በዳሳሽ አሞሌ ውስጥ የሚታይ ስም ነው።

አንድን ክላሲፋየር ለማጥፋት ከዝርዝር ውስጥ ምረጥ እና “ክላሲፋየር አስወግድ” የሚለውን ተጫን።

ለክላሲፋየር አንድን ግቤት ለመቀየር፣ ከዝርዝር ውስጥ ምረጥ እና “ክላሲፋየር ወቅር” የሚለውን ተጫን (ወይም በዝርዝር ውስጥ ያለውን ክላሲፋየር ሁለት ጊዜ ጠቅ ጠቅ አድርግ)።

የክላሲፋየሮቹ ቅደም ተከተል በዳሳሽ አሞሌ ውስጥ ባለው ቅደም ተከተል የታያል። ለመለወጥ፣ ክላሲፋየሩን በመምረጥ "Move Up" እና "Move Down" ቁልፎችን ይጠቀሙ።

ስለ ክላሲፋየር ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የግሪንስቶን አደራጅ መምሪያ ምዕራፍ ሁለት - Getting the most out of your documents አንብብ።