7.3: እይታ በኤክስፐርት ሁነታ ፍጠር

በኤክስፐርት ሁነታ “ምዝግብ ማስታወሻ መልዕክት” በመጠቀም በግራ በኩል በፊት ክምችቱን ለመገንባት የተኬደውን አካሄድ ለማየት እና ስኬታማ መሆኑን ወይም አለመሆኑን ማወቅ ይቻላል። የምትፈልገውን የምዝግብ ማስታወሻ ከ“ምዝግብ ማስታወሻ ታሪክ” ዝርዘር ውስጥ ምረጥ።

በዚህ ሁነታ፣ ሙሉ የማስገባት እና የመገንባት ዝርዝር አማራጮች በግራ በኩል ይቀርባሉ። የተለያዩ አሰራሮች እንደ “ግቤቶችን መወቀር” መስኮት በየሰነድ ፕለጊኖች ክፍል በተገለጸው መሰረት ይሆናል። አንዳንድ መስኮች የቁጥር ግቤት ሲያስፈልጋቸው እነዚህን በመፃፍ ወይም አሁን ያለውን ዋጋ ለመጨመር ወይም ለመቀነስ ቀስቶችን መጠቀም ይችላሉ (አንዳንዴ የሚሰጡት የዋጋ መጠን የተገደበ ይሆናል)። ሌሎቹን ለማንቃት አመልካች ሳጥኑን መጫን ላማፍዘዝ ደግሞ እንደገና መጫን ያስፈልጋል።

ስለ ክምችት ማስገባት እና መገንባት ተጨማሪ ማብራሪያ ከየግሪን ስቶን አደራጅ መምሪያ- የክምችት ግንባታ ሂደት መገንዘብ (Understanding the collection-building process ) የሚለውን ምዕራፍ አንድ ተመልከት።