8.2: አጠቃላይ |
ይህ ክፍል በክምችትህ ውስጥ ያሉትን አጠቃላይ ቅንብሮች ለመከለስ እና ለመለወጥ እንዴት እንደሚቻል ያሳያል። በመጀመሪያ በ“ቅርጸት” ትብ ስር “አጠቃላይ” የሚለውን ተጫን።
እዘህ አንዳንድ በክምችት ደረጃ ሜታዳታ ሊዘጋጅ ወይም ሊስተካከል ይችላል፣ አዲስ ክምችት ሲፈጠር የገባ ርዕስ እና ገለጣ ጨምሮ።
በመጀመሪያ የክምችቱ ፈጣሪ እና ጠጋኝ ኢሜይል አድራሻ ያጋጥማል። የሚከተለው መስክ የስብስቡን ርዕስ ለመቀየር ያስችላል። ስብስቡ የተጠራቀመበት አቃፊ ቀጥሎ ይታያል፣ ነገር ግን ይህ ግን አይለወጥም። ከዚያ በክምችቱ አናት በስተግራ በኩል “ስለ” የሚል ገጽ (እንደ ዩአርኤል አይንት) ይታያል። ቀጥሎ ወደ ክምችቱ የሚያገናኝ አዶ በግሪንስቶን ላይብረሪ ገፅ ውስጥ ይታያል። ከዚያም ክምችቱ ለህዝብ ይፋ እንዲሆን ወይም እንደይሆን የሚያረጋግጥ ሳጥን ይታያል። በመጨረሻም “ክምችት ገለጣ” የፅሁፍ ቦታ በአዲስ ክምችት መፍጠር ይታያል።