1.1: ከመዳፊት እና ምናሌዎች |
በዚህ ክፍል መሰረታዊ የላይብረሪያን በይነገጽ አጠቃቀሞችን ይገለፃል። እንደ ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር ወይም ማይክሮሶፍት ኦፊስ ፕሮግራሞች ጋር ትውውቅ ካለህ እና የመዳፊት እና ምናሌዎችን አጠቃቀምን ጠንቅቀህ ካወቅህ ወደ ይህ ሰነድ እንዳይነበብ እንዴት ማገድ እንደሚቻል ተሻገር።
የላይብረሪያን በይነገጽ የማይክሮሶፍት ዊንዶው የሚከተል እና በዊንዶው እውቀት ላይ የተመሰረተ ነው።
ማንኛውም የምትሰራበት የስክሪን አካል ለምሳሌ ቁልፍ ወይም የመፃፊያ ቦታ “መቆጣጠሪያ” በመባል ይታወቃል። በማንኛውም ጊዜ አንድ መቆጣጠሪያ “ፎከስ” ተደርጎ ከኪቦርድ ጋር ይተዋወቃል። ብዙ መቆጣጠሪያዎች ጠቆር ያሉ ሰማያዊ አካላትን ለመምረጥ እንዲታዩ ይደረጋል። አንዳንድ መቆጣጠሪያዎች በግራጫ ቀለም የሚታዩት ስራ ላይ እንዳልሆኑ ለማሳየት ነው።
እንደተለመደው መዳፊትን ወደ-ግራ ወይም ወደ-ቀኝ ጠቅ በማድረግ መጫን ይቻላል። ብዙ አካላቶችም “ጎተት” ለማድረግ የስችሉሃል፤ የመዳፊትን የግራ-ቁልፍ ተጭኖና ያዝ በማድረግ፣ መዳፊቱን ማንቀሳቀስ፣ እና ቁልፉን በመልቀቅ ሌላ ቦታ መጣል። አንድ አካል በላያቸው ላይ ሲያንዣብብ .... እይታቸው ይቀየራል።
የጽሁፍ ፊልዶችን ለመጻፍ ኪቦርድ መጠቀም ይቻላል፡፡ ታብ የሚለውን በመጫን አንድ ሰው ወዳሉት ፅሁፎች ማለፍ ይችላል፡፡
የላይብረሪያን በይነገጽ ፕሮግራም ለመዝጋት “ፋይል“ ከሚለው ዝርዝር ውስጥ “መውጫ” የሚለውን ምረጥ። መጀመሪያ ክምችትህ ዲስክ ላይ ይቀመጣል።