2.3: ያለውን ክምችት መክፈት

ያለውን ክምችት ለመክፈት ከ”ፋይል” ምናሌ “ክፈት”ን በምረጥ የክምችት መክፈቻ ማስታወቂያ ይመጣል። ከዚያም የግሪንስቶን ክምችቶች ይታያሉ። አንዱን በመምረት ገለጣውን ተመልከት፣ “ክፈት” ጠቅ በማድረግ ክምችቱን መጫን ይቻላል።

በአጋጣሚ ከአንድ በላይ የሆኑ የግሪንስቶን ላይብረሪያን በይነገጽ ፕሮግራም በተመሳሳይ ጊዜ ስራ ላይ ከሆነ፣ ተገቢ ማውጫዎች ችግር እንዳይፈጠር የቆለፋሉ። አንድን ክምችት ስንከፍት ጊዜያዊ የመዝጊያ ቁልፍ ምልክት አቃፊው ላይ ይፈጠራል። አንድን ክምችት ከመክፈት በፊት የላይብረሪያን በይነገጽ የተዘጋ ፋይል አለመኖሩን ያረጋግጣል። ነገር ግን ላየይብረሪያን በይነገጽ ከመከፈቱ በፊት ከተዘጋ (ያለ አግባብ ከተዘጋ) የተቆለፈው ፋይል አልፎ አልፎ እንዳለ ይቀራል። እንደዚህ አይነቱን ክምችት ሲከፈት የተቆለፈ ፋይልን "'በስርቆት" መቆጣጠር እንደምተፈልግ ይጠይቅሃል። ይህንን ለመምረጥ ሌላ ሰው በተመሳሳይ ክምችቱ ላይ እየሰራ እስካለሆነ ድረስ ለመምረጥ ነፃ ሁን አያሳስብህ።

የግሪንስቶን ላይብረሪያን በይነገጽ ያልፈጠረውን ክምችት ሚከፈትበት ጊዜ የዱብሊን ኮር ሜታዳታ ስብስብ ስያሜ የገኛል፣ እና ቀደም ብሎ ያለው ማንኛውም ሜታዳታ ልክ ባለው ሜታዳታ ፋይሎችን ድራግ ሲደርግ እንደሚገባ ሁሉ። ይህንን ሂደት ይበልጥ በፊት የተሰጠ ሜታዳታ ማስገባት ክፍል ውስጥ ተብራርቷል።