9.1: ምርጫዎች |
ይህ ክፍል የምርጫዎችን መገናኛ የሚገልፅ ሲሆን ይህም ሚገኘው “ፋይል” --> “ምርጫዎች” በመክፈት ነው።
የምርጫዎች መስኮት የሚከፈተው “አጠቃላይ” በሚለው ትብ ነው። የመጀመሪያው አማራጭ የኢሜይል አድራሻ የሚገባበት መፃፊያ ቦታ ነው። ይህም ለአዲስ ክምችቶች “ፈጣሪ” እና “ጠጋኝ” ሜታዳታ ስብስብ ዓይነቶች የሚውል ነው። ሌላው አማራጭ በቋንቋዎች ዝርዝር የላይብረሪያን በይነገጽ የሚታወቅበት ነው። አንዱን ከዝረዝሩ በመምረጥ ቋንቋውን ከቀየርህ ላይብረሪያን በይነገጽ በራሱ እንደገና ጀምሮ አዲሱን ቋንቋ ይጭናል። እንዲሁም የቅርጽ ቁምፊ መወሰኛ የጽሁፍ ሳጥን ይቀርባል፤ ዩኒኮድ ለማየት ጥሩ አሰራር “አሪያል ዩኒኮድ ኤምኤስ፣ ቦልድ፣ 14” ነው።
“የተገኘ ሜታዳታ እይ” ከተመረጠ፣ የተለያዩ ሜታዳታ ጋር የሚሰሩ መቆጣጠሪያዎች ከሰነዶች የተገኙ ሜታዳታዎችን ምንግዜም ያሳያሉ። እንዳይመረጥ ማድረግ ይህን ሜታዳታ ይደብቃል። (ምንም እንኳን በክምችት ነደፋ እና በመጨረሻው የግሪንስቶን ክምችት ላይ ቢኖርም) “የፋይል መጠን አሳይ” ከተመረጠ የፋይሉ መጠን ከእያንዳንዱ ፋይል ቀጥሎ በስራ ቦታ የሚታይ ሲሆን የክምችት ፋይል ቅርንጫፎች መሰብሰቢያ እና ማበልጸጊያ እይታ የታያሉ።
የ“ሁነታ” ትብ በበይነገጽ ውስጥ በዝርዝር ተቆጣጥሮ ለመጠቀም ያስችላል።በዝቅተኛ አቀራረብ “ላይብረሪ አሲስታንት” የንድፍና ቅርጽ እይታዎች ስራ ላይ አይሆኑም። ተጠቃሚው ሰነዶችን መጨመር ወይም መሰረዝ የሚችል ሲሆን ሜታዳታ መጨመር/ማስተካከል እና ክምችቱን እንደገና መገንባት ይቻላል። የፍጠር ፓነሉ በቀላሉ የተቀመጠ ነው። “ላይብረሪያን” ሁነታ ለሁለም ንድፍ እና ቅርጽ ለማየት የሚያስችል ሲሆን የፍጠር ፓኑ ይልተወሳሰበ ነው። “ኤክስፐርት” ሁነታ ሙሉ የፍጠር ፓን ያለው ሲሆን የክምችት አጠቃላይ ውጤቶችን በሎግ ውስጥ እንዲመዘገቡ ያደርጋል። ሁነታዎችን ለመለወጥ ወይም ለመከለስ ከሁነታ ቀጥሎ ያለውን ሬዲዮ አዝራር በመጫን ይሆናል። ያሉበትን ሁነታ ለማየት የላይብረሪያን በይነገጽ የርዕስ ቦታውን መመልከት ይችላል።
የ“ተያያዥ” ትብ እየሰራ ያለውን አካባቢያዊ የግሪንስቶን ላይብረሪ አገልጋይ ዱካ ለመቀየር የሚያስችል ሲሆን አጠቃቀሙም ክምችቶችን በምናይበት ጊዜ ነው። እንዲሁም የኢንተርኔት ግንኙነት ለመፍጠር የእጅ አዙር መረጃ የሚሰጥ ነው። (ለምሳሌ፡ ፋይሎችን ስናወርድ ፋይሎችን ከኢንተርኔት በማውረድ ላይ የሚለውን ክፍል አንብብ። የእጅ አዙር ግንኙነት ለመፍጠር ሳጥኑን በማየት ዝርዝር መረጃ ስጥ (አድራሻ እና የፖርት ቁጥር) ስት። የዕጅ አዙር ግንኙነቱ የሚሰራው ታዲያ የምርጫዎች መጋናኛ ሲዘጋ ነው።
ዕየሰራ ባለበት ጊዜ የላይብረሪያን በይነገጽ ለሚወስዱ እርምጃ የሚከተለው ሁኔታ ምን እንደሆነ ያስጠነቅቃል። ይህንን መልዕክት ለማስተው “ይህን ማስጠንቀቂያ ድጋሚ አታሳይ” የሚል ሳጥን ይመጣል። የ“ማስንጠንቀቂያ” ትብ በመጠቀም የማስጠንቀቂያ መልዕክቶችን እንደገና ማምጣት ይቻላል።