4.6: ፋይሎችን ማስወገድ

ፋይሎችን እና አቃፊዎችን የምናስወግድበት ብዙ ዘዴዎች አሉ። በመጀመሪያ የሚወገዱትን ፋይሎች አና አቃፊዎች በ የመሰብሰቢያ እይታ እንደተጠቀሰው ለይ።

አንዴ ፋይሎች ከተመረጡ፣ “ሰርዝ” የሚለውን ቁልፍ መጫን፣ ወይም በቁልፍ ሰሌዳ ላይ የ [Delete] ቁልፍን መጫን፣ ወይም ከክምችት ውስጥ በመጎተት ወደ ሰርዝ ቁልፍ ወስዶ እዛው መጣል።