4.1: የመሰብሰቢያ እይታ

በዚህ ክፍል የመሰብሰቢያው ቦታ ላይ የሚገነቡት ክምችቶች ውስት የሚካተቱትን ፋይሎች ለማየት ያስችላል። የላይብረሪያን በይነገጽ የሚጀምረው በመሰብሰቢያ እይታ ነው። ለወደፊቱ ወደዚህ እይታ ለመመለስ "Gather" የሚለውን ከምናሌ አሞሌ በታች ያለውን ትብ መጫን ነው።

ሁለቱ ሰፋፊ ይዘት ያላቸው “የስራቦታ” እና “ክምችት” የሚባሉት ፋይሎችን ወደ ክምችት ለማንቀሳቀስ ይጠቅማሉ።እነዚህ ፋይሎችን እና አቃፊዎችን የያዙ "የፋይል ቅርንጫፎች"ን ይወክላሉ።

በዛፉ ውስጥ አይነቱን አንዴ ጠቅ በማድረግ ምረጥ። ወይም አቃፊውን ሁለት ጊዜ ጠቅ ጠቅ ማድረግ፣ ወይም የማጥፊያ ምልክቱን አንድ ጊዜ በመጫን ማስረዘም (ወይም ማሳጠር) ይቻላል። ፋይሉን ሁለት ጊዜ ጠቀ ጠቅ ማድረግ እና ተያያዥ ፕሮግራም ተጠቅሞ መክፈት ይቻላል (ፋይልን ማዛመድ ተመልከት)።

የስራቦታ ፋይል ቅርንጫፍ ለላይብረሪያን በይነገጽ የሚሆነውን የዳታው ምንጭ - አካባቢያዊ የፋይል ስርዓት (የዲስክ እና ሲዲሮም ድራይቭ ጨምሮ) ያሉትን የግሪንስቶን ክምችቶች እና ዳውንሎድ የተደረጉ የፋይሎች ካች (cache) ያሳያል። እነዚህን ፋይሎች ኮፒ አድርጎ ማየት የሚቻል ሲሆን ወደ ሌላ ቦታ ማዛወር፣ ማጥፋት ወይም ኤዲት ማድረግ ግን አይቻልም። ነገር ግን ዳውንሎድ የተደረጉ ፋይሎች ማጥፋት ይቻላል። በዚህ ቦታ ላይ በመሄድ በክምችቱ ውስጥ መካተት ያለባቸውን ፋይሎች መምረጥ ይቻላል።

የክምችት ፋይል ቅርንጫፍ ከዚህ በፊት የተሰሩትን ክምችቶች ያሳያል። መጀመሪያ ላይ ይህ ቦታ ባዶ ነው።

ቦታውን እንደገና በማውስ ግራጫ ባር ላይ በማድረግ መጠኑን በማስተካከል ቅርንጫፎችን መለየት (የአመልካቹ ቅርፅ ይለወጣል) የሚቻል ሲሆን ይህም ለመጎተት ያስችላል።

በዊንዶው ታችኛው ክፍል ፋይሎችን በተመለከተ ስለተወሰደው እርምጃ (ማለትም ኮፒ ለማድረግ ወደ ሌላ ቦታ ለመውሰድ እና ማጥፋት) የሚያሳይ ነው። እነዚህን ለማጠናቀቅ የተወሰነው ጊዜ ይፈጃል። የ"አቁም” ቅልፍ በሂደት ላይ ያለውን ማንኛውንም ስራ ለማቆም ይረዳል።

ሁለት ትልልቅ በተኖች የስክሪኑን ታችኛው ቀኝ ክፍል ይይዛሉ። “አዲስ አቃፊ” የሚለው፣ ምስል ከያዘ አቂፊ ጋር አዳዲስ አቃፎዎችን ለመክፈት ይረዳል። ( አቃፊዎችን መፍጠር ተመልከት። “ሰርዝ” የሚለው የቆሻሻ መጣያ ምልክት ያለው ፋይሎችን ለመሰረዝ ይረዳል። የማጥፊያ በተኑን መጫን ከክምችቱ ውስጥ የተመረጡትን ፋይሎች ያጠፋል። እንደአማራጭ ፋይሎችን ወደ ስርዝ ቁልፍ በመጎተት ማጥፋት ይቻላል።

የተለያዩ ቅደም ተከተል ያላቸውን ነገሮች ለመምረጥ፣ የመጀመሪያውን መምረጥ እና ከዚያ ወደታች በመግፋት (የሺፍት ቁልፍን በመያዝ) እና በመጨረሻ ምርጫው ሁሉንም የተመረጡትን አጠቃሎ ይይዛል። ቅደም ተከተል የሌላቸውን ፋይሎች ለመምረጥ (ኮንትሮል ቁልፍን በመያዝ) ወደታች መግፋትና መጫን። እነዚህን ሁለቱን ዘዴዎች በጋራ በመጠቀም የተለያዩ ፋይሎችን መምረጥ ይቻላል።